ወደ ኮሌጅ ልጅን መላክ

የሰባት አመት ልጄን የበጋ ወራት የመፅሃፍ ቅዱስ ካምፕ ላደርሰው ሻንጣውን ይዞ ከቤት ስንወጣ ነፍሴ ድንገት ከውስጤ የወጣች መሰለኝ የምንኖርበትን ቤት በር እንክዋን አልዘጋሁም ልጄ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ። ጊዜና ቦታ በማይገድበው ምእናብ ልጄን ኮሌጅ ሲሄድ አየሁት ፣ በኮሌጅ ትምህርት ቢዚ ሲሆን ሊያወራኝ እንክዋ ጊዜ የለኝም ሲል። ጊዜ ፍጥነቱ!!

ትምህርት ጨርሶ እቤት ይመጣል ብዬ ላስብ ስሞክር አይ አይደለም ስራ ይይዘዋል ከአገር አገር፣ ከቢሮ ቢሮ፣ ታላላቅ ጉዳዮችን ሊፈፅም ይሮጣል። ልጄ ናፈቀኝ!!

እንዴ እንዴ በቃ እንዲህ ነው ድንገት ሳልዘጋጅ ልጄ ከእጄ የሚወጣው? የልጄ በፍጥነት ማደግ ማስረጃ ሆነው ከፊቴ ተደረደሩ: እውነት ነው ጨቅላ ሆኖ እጄ ላይ የተንከባለለበት ቀን እና ዛሬ የደረሰበት እድሜ በምን ጊዜ እንደደረሰ በትክክል አይገባኝም በጣም ቸኩሎብኛል።

አውቃለሁ ይህ ብላቴና በጎበዝ እጅ እንዳለ ቀስት ነው ተወርውሮ አላማውን ይመታል። ደግሞም ይወጣል ይወርሳል ያሸንፋል።

ለእኔ ግን ዛሬ ናፍቆት በሆዴ ውስጥ ገባ ልጄ እንዳይሄድብኝ ፈለኩ: አይን አይኑን አያለሁ የያዘውን ሻንጣ አያለሁ። ላስቀረው? እድሜው ገናነው ምን አስቸኮለኝ? ይቅር እቤት ውስጥ ይቀመጥ ልቤ አማራጭ ሰጠኝ። አይ ይሄማ ለእድገቱ ውሳኝ ነው ዛሬ ህይወቱ ላይ የዘራሁት ነው ነገ ተፅእኖ የሚያመጣው። ክርክር ውስጥ ገባሁ. “ማም!! ” ልጄ ቀሰቀሰኝ : “በር እየዘጋሁ ነው መጣሁ” መለስኩለት። ምን ሆናለች ዛሬ እናቴ ሳይል አይቀርም አስተያየቱ ያስታውቃል

ተንደርድሬ አቀፍኩት ሳምኩት፣ እወድሃለሁ እሺ እሺ!፣ “እ” መልሱ ነበር። ” ቃል ግባልኝ” ጠያቂ ሆንኩ. “ዋት?” ነገሬ የገረመው ልጄ. “አሁን እኮ ትልቅ ልትሆን ነው ኮሌጅ ልትገባ ልትማር ስራ ልትይዝ በቃ ጊዜ አይኖርህም።” ልጄ የማወራውን በግልፅ ይግባው አይግባው አላውቅም ነገር ግን የልቤን ጭንቀት መተንፈስ ቀጠልኩ። ስለዚህ አደራ እንድትደውልልኝ እሺ “ኖ!! አም ጎነ ቢ ቢዚ” የልጄ መልስ ነበር። “ትናፍቀኛለህ እኮ እባክህ?” “ማም!” ስምንት አመት እንክዋን ካልሞላው ልጄ ጋር ድርድር ያዝኩ ቀኑ ሲደርስ ከማለቅስ በጊዜ ብለምን ይሻለል ብዬ።

ምሳሌ 22: 6 ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።

በዚህ ውስጥ ነፍሴ ሌላ ነገር አስተዋለች በልዩ ልዩ ነገር ዛሬ ቢዚ ሆኜ የማይመለስ ውድ ጊዜ ከልጄጋር ማሳለፌን እንዳያመልጠኝ ፣ እንድደሰትበት ዋጋ እንድ ሰጠው። ነገ የልጄ ቀን ነው እርሱ ተራውን የሚሮጥበት የሚወርስበት ነውና የእርሱን ጊዜ መሻማት ሳይሆን የእኔን ጊዜ በአግባቡ መጠቀምን ተማርኩ።

እየተነጋገርን አሳንሳር ውስጥ ገብተን መኪናዬ ጋር ደረስን። አምላኬ ታማኝ እና እውነተኛ ነው ታላቅና ሃይለኛ ነገር በዚህ ልጅ ያደርጋል። ቀኑ ሲደርስ እኔንም ይረዳል።

እናንተስ ልጃችሁ የቱጋር ነው ያሉት? የትስ እንዲዱ ታያላችሁ?

ነፃነት

Leave a comment