ብዙ ጊዜ ወደ አምላካችን ስንጠጋ ወይንም በራልኝ፣ ተረዳሁ ፣ ገብቶኛል እያልን ስንል የገባን ምንአልባትም የጠቅላላውን እውነት ጥቂቱን ብቻ መሆኑን ለማየት ጊዜ ይወስድብናል ወይንም ደግሞ የዛን እይታ ትልቅ ክፍል እንዳለው ለማመን ይከብደናል። እውነቱ ግን ይህ ነው።
ከእውቀት ከፍለን እናውቃለን።
ምንም ያክል ሊቅ ጠቢብ ብንሆን ወይንም የሃይማኖት ጥናት ብናደርግ አምላክ ታውቆ አይጨረስም። አምላክ አምላክ ነውና እንክዋን እርሱን በሙሉ አውቆ ለመጨረስ የፈጠረውን አንድ ፍጥረት እንኳን ለማጥናት ዘመናት ይፈጃል። ለዚህ አይደል ሳይንቲስቶች ዛሬም ስራ ያላቸው! ፍጥረት እስካለ የሚጠና ነገር ይኖራልና።
ወደ ተነሳሁበት ልመለስና እውነት እውነት ግን ምን ያክል ነው የበራልን? ምን ያክል ነው የተረዳነው? የአምላክ ልጅ ነኝ ብሎ አንድሰው በምድር እየተመላለሰ ነገርግን አንድም የአባቱ ሁኔታ በእርሱ ላይ መገለጥ ካልቻለ በእርግጥ ልጅ ነው ማለት እንችላለን? ይህን ሁኔታ በምን ገምግመን ነው አዎ የአምላክ ልጅ ነው ማለት የምንችለው? ለምሳሌ አንድ ልጅ አባቱን በመልክ ሊመስል ይችላል ቁርጥ አባቱን ነው ይላሉ የአገሬ ሰዎች። ወይንም የአባቱን ሃብት ያለመከልከል ሲጠቀም ብናይ አለያ ይህ ሰው ጥፋት አጥፍቶ ሲይዝ አባቱ ዋስ ከፍሎ ሲያስፈታው ስናይ ከሌላው ሰው የሚለይበት ነገር እናያከን። ምንአልባትም እንክዋን ያለ አግባብ ያባቱን ሃብት ቢበትን አንተ እንዴት በተንክ ብሎ የሚጠይቅ የውጪ ሃይል የለም። ምክንያቱም ይህ በአባትና ልጅ መካከል የሚደረግ ውይይት ነውና ሌላው ሰው አያገባውም።
ታዲያ ግን ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የልጅነት ስልጣን ሰጣቸው ተብሎ ተፅፎ ሳለ ። ልጅ ነኝ የሚለው ጉዳይ ምንው ለብዙ ዳግም ተወላጅ ቃል ብቻ ሆነ? ለዚህ ነው ጥያቄው ያነሳሁን የተገለጠልን በከፊል ብቻ ነው መሰል? ልጅ ከሆንክ/ሽ አዲስ ዘር ውስጥ ገብተሃል/ሻል። አባት ያለውን ሁሉ ነህ/ሽ።
ይህ እውነት ከሲኦል ማምለጥ አንዱ ጅማሬ ሲሆን ደግሞም አምላክን መምሰል ፍፃሜው ነው። በእነዚህ ሁለት ጥጎች ውስጥ የትኛው ጋር ደርሳችሁ ይሆን?
ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፡— እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
Then said Jesus unto them again, Verily, verily, I say unto you, I am the door of the sheep.
ዮሐንስ 10:7
ነፃነት Nov, 19 2022






