ምን እጃችሁ ላይ አለ? እርሱ እመጣለሁ ብሎ የዘገየ በሚመስለበት በዚህ ሰአት እርሱ የሚከፍለውን ደሞዝ ይዞ ሲመጣ ማንን ያገኝ ይሆን ምንስ በእጅ ላይ ይገኝ ይሆን?
ስራ የተሰጥን እንድናበጅ እንድናስተዳድር ተንከባካቢ እንድንሆን እንድን ጠብቅ ነው ይህ ከሰማይ ያለው ሃሳብ ነው። መስተዳድር ተብሎ በተሰጠህ ላይ ምን ያክል ሰርተህ ይሆን? በአንተ በእንቺ ውስጥ ስራ ግን ምን አይነት ትርጉም ይኖረው ይሆን? ምን አይነትስ ስራስ እየሰራሽ አለቃሽ ያገኝሽ ይሆን?
ገንዘብ መውደድ የሃጥያት ሁሉ ስር ነውና የምናሳድደውን ብናውቅ መልካም ነው ገንዛብ ለማግኘት ፪፬ ሰአት ስትሮጥ ውለህ አድረህ ድንገት የደረስክበት ሲመስልክ ከእጅ አፈትልኮ እንደ ምርጥ እየመሰለ በብዙ ምኞት እና ሃሳብ በማናወዝ ከተፈጠርክለት የመግዛት ስፍራ ያወርድህና ባርያ ያደግሃል። አለቃህንም በትጋት እንዳትጠብቅ ያሳስታል።
ትዳር ብዙ ወገኖኝ በብቸኝነት ዘመናቸው ፈጣን ሯጭ ናቸው ትዳር ውስጥ ሲገባ ቀዝቀዝ ማለት መጀመሩ መልካም ቢመስልም ለብዙዎች ግን ጭልጥ ብሎ መተኛ ይሆናል። ንቃ ንቂ ትዳርሽ በእርግጥ በጌታ ፊት የምትሸለሚበት ቢሆንም የእርሱን ስራ ግን እርግፍ አድርገህ /ሽ እንድትተዊው አልነበረም የሰጠህ።
ድካም በሁሉ ቤት ያንኳኳል ካለብን ጫና ወይም ከወደቀ አለም ግፊያ የተነሳ እርሱም ቢሆን ግን ከመንቃትና ከመጠበቅ አይከለክልም
ምንድን ይሆን ያደከመህ ስራህን እንዳትሰራ ያስደረገህ? እኔ ግን ድንገት በክብሩ ቢገለጥ ስራ ላይ ሆኜ ያገኘኛል አታንቀላፋ አታንቀላፊ ጊዜው በረዘመ ጊዜ ተስፍሽ የበለጠ ይታደድ እንጂ አትዘናጊ።
ዘፍጥረት 1:28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፡— ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
ነፃነት