እውነትን መናገር

በመንገድ ላይ ካየሁት ተነስቼ ብቻ ባወራ በእርግጥ የልምዴን እናገር ይሆናል ይህ ብቻ ግን የታሪክን ሙሉ እውነት አይገልፅም። አንዳንዱን እንደውም ስለረሳሁት ወይንም ላያስፈልግ ይችላል ከሚል ግምት ልዘለው እችላለሁ። ገጥሞአችሁ ያውቅ ይሆን የሆነ የምታውቁት ሰውን መንገድ ላይ አይታችሁት: ምን አልባት በርቀት ወይም በችኮላ ይሆንባችሁና ሳታናግሩት አልፋችሁ። ያን ሰው ስታገኙት በዚህ ቀን እዚህ ቦታ አየሁህ ስትሉ ያሰው በፍፁም በዛ ስፍራ እንዳልነበር ሲያስረዳችሁ? ወይንም እንዳያችሁት ስልክ ደውላችሁ እያየሁህ እኛ ለፍከኝ እንዲህ ቦታነኝ ስትሉ ያሰው ጭራስ ሌላ ክፍል ስፍራ መሆኑን ሲያረጋግጥላችሁ። ታዲያ ምን ትንሽ ፈጠረ? ያያችሁት ማንን ነው? ብዚ ጊዜ እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ዝም ብለን እንደ ተራ እናልፋቸዋለን። ነገርግን በእርግጥ ብናስተውላቸው ሌላ እውነት አላቸው ተምረባቸው እንድናልፍ የሚጠበቅ እውነት። ያየነው ብቻውን በቂ አይደለም።

አስታውሳለሁ የህግ መፅሃፍትን አገላብጥ ዘንድ እድል በነበረኝ ወቅት መምህራችን እንዲህ ይል ነበር “መስመሩ ላይ ያለውን ብቻ እኛ ታንብቡ ከመስመሩ በታች፣ ከመስመሩ በላይ ከመስመሩ በስተጀርባ የተፃፈውን ፈልጉ” እንዴት ያለ ትእዛዝ ነው? እኔ “የተፃፈውን እንጂ ያልተፃፈውን ከየት አምጥተን እናነባለን?” ያው መምህር ስለሚከበር በፊቱ አላጉረመረምኩም በልቤ እንጂ ።

በእርግጥም እውነት ለካ እንዲህ ናት አንዳንዴ ፊትለፊት ያለው የተገለጠው ብቻ ሳይሆን ያልተገለጠ የሚመስል ነገርግን ግልጥ የሚመስለውን የሚመራ እና የሚያስተናብር እውነት አለ።

በህግ ትምህርት ላይ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ለማየት ህግ አውጪዎቹ እነማን ናቸው? መቼ ነው ይህግ የወጣው? በዚህ ህግ መውጣት ጊዜ ምን ምን አይነት ክርክሮች ውይይቶች ተደርገው ነበር? ይህ ከመውጣቱ በፊት በምን ሁኔታ ነበር ጉዳዩ የሚታየው? ወደፊትስ ሊሸፍን የሚፈልገው ክልል አለወይ? እንግዲህ አንድ ህግ የሚለውን ለማወቅ ነው ይህ ሁሉ ምርምር: በእርግጥም በጥንቃቄ መረዳቱ ለሎሎች ህይወት ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችል አቅም ነውና ትክክለኛው ሃሳብ ማግኘት ግድያደርገዋል።

በህይወት ውስጥም እውነትን መፈለግ ከዚህ የባሰ ዝርዝር እይታ ይጠይቃክ ። ፊታችን ላይ እየሆነ ያለውን ብቻ ሳይሆን ከዛ አልፈን ማየት ይጠይቃል። ግለሰቦችን በውሳኔዎቻቸው እንዳንፈርፍባቸው ወይም የራሳችን እርምጃዎች ጠባብ በሆነ መንገድ ውስጥ እንዳይገኝ እውነትን መከታተል መልካም ነው።

የሐንስ 8:32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።

Leave a comment