እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ

ይድረስ ለምወድህ እና ለማከብርህ እግዚአብሔር: እኔ ደህና ስለሆንኩና ስለተጠብኩ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ላይ ስልጣን ያለህ እንደሆንክ ስለማውቅ በደስታ ይህን እፅፍልሃለሁ።

My letter to you Lord

ለመሆኑ በህይወት መዝገብ ውስጥ ቀላል የሚባል የህይወት ጉዞ አለን? እንደው መንገዱ አልጋ በአልጋ የሆነለት ማን ይሆን? እኔን አይመስለኝም እያንዳንዱ ሰው የሚያልፍበት መንገድ የራሱ ኮረብታ ቁልቁለት ሜዳ ይኖረዋል። ” የ ይስሐቅን ህይወት ተመልክቼ ከ ወገኖቹ አንፃር ሲታይ ቀለል ያለ ህይወት የኖረ ይመስላል ነገርግን በደንብ ሲታይ ብዙ ግፊያ የነበረበት ህይወት ነው ። ማሳረፍን እምታውቅ አንተ ብታሳርፈውም”

በእርግጥ ለአንዳንዶቻችን ከባድ የሚመስሉ መንገዶች ይሰጡን እና እንዴት እንደምናልፋቸው ስንጨነቅ ገና ቀኑ ሳይደርስ ሃይላችንን እንጨርሳለን። የትግስትን ፍሬ ለማየት የቻለ ምንኛ እድለኛ ነው። “የዳዊት ህይወት ያሳዝናል በብዙ ስደት ፣ መገፋት፣ ከሞት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ነው። ምንአልባት በነዚህ የስደት ዘመናት ይህ ሰው መጠራቱን መቀባቱን ተጠራጥሮ ይሆናል: የመከራው ርዝመት ተስፋ የሚያስቆርጡ ወቅቶች ጋር መጋፈጡ ቀላል አልነበረም ነገርግን አምላክ ከተናገረው ህይወቱ ላይ ያልተከናወነ አልነበረም ”

እኔ እራሴ ነገር ቀለል ብሎልኝ የኖርኩባቸውን ዘመናት አስብና እንዴት እግዚአብሔር መልካም ነው እላለሁ : በዛው ልክ አላልፍም ብዬ ተስፋ የቆረጥኩባቸው ተራሮች ጋር እፋጠጣለሁ በዚህኛውም እግዚአብሔር መልካም ነው። የተራራው መትለቅ ወይም ማነስ ሳይሆን የአምላክ ማንነቱ ስለሆነ ስልጣን ያለው በዚህ ተስፋ ደስ እሰኛለሁ።

ቆይ ግን ደብዳቤው ለእግዚአብሔር አልነበር እንዴ መፃፍ የጀመርኩት እንዴት ሆኖ ነው የህይወት ውጣ ውረድ መዝገብ ውስጥ የገባሁት ? ለነገሩ ህይወትን እራሱ የያዝከው አንተ ስለሆንክ በውስጡ ያከሁት እኔ የገባኝን ባወራልህ ትክክል እንጂ ስህተት አይሆንም።

Leave a comment