ይቅርታን መቀበል

ሰዎች መጥተው ይቅርታ ቢጠይቁአችሁ መልሳችሁ ምን ይሆን?

ሰዎችን ይቅር ብዬሃለሁ ማለትና መተው መታደል ነው። በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ እግዚአብሔር ይቅርታን እሚያስተምረኝ ዘመን ነበር እና የተለያዩ ሰዎችን ይቅርታ እንድጠይቅ ያስተምረኛል እናም አንድ ሰውን ይቅርታ መጠየቅ ነበረብኝ ስለዚህ ሄድኩ ሳገኘው ይቅርታ እንድታደርግልኝ ፈልጌ ነው ይቅርታ አልኩ። ያሰው በጣም ተናደደ የማይሆን የማይሆን ነገሮችን ተናገረ ጭራሽ ነገሩ የባሰ የሆነ መሰለ። በዚያን ወቅት እኔ ብዙም አልጨነቀኝም ነገሩን ተቀበለው አልተቀበለው ሳይሆን እኔ ሄጄ ይቅርታ ማለቴ ብቻ ነበር ግዴታ አድርጌ ያሰብኩት። ምንአልባት አሁን ቢሆን ለዛ ሰው የተለየ መራራትና ሃዘኔታ ግድ ማለት ይበዛልኝ ነበር።

ጊዜያት አለፉ በተለያየ ጊዜ ይቅርታ መጠየቅና ይቅር ማለት የህይወቴ ክፍል ሆኖ ቀረ ። ከሰው ጋር ስንኖር ሊያሳዝኑን ቢችሉ ይቅር ብሎ መተውን የመሰለ ልብን የሚያሳርፍ ነገር እንደሌለ አውቄያለሁ። የሁለችን አይኖች በተከፈቱና ይህን ማየት በቻልን። ከይቅርታ የሚበልጥ የነፃ መውጣት ሚስጥር የለም።

እናም ዛሬ ይህን የምፅፍበት ምክንያት መጣ የኔ የሆነሰው አሳዝኖኝ ነበርና ትንሽ ከፍቶኛል ታዲታ ያሰው ደውሎ ይቅርታ በቀደም አሳዘንኩሽ ማለት፡ የሚሰማው ጆሮዬ ንግግሩን በትክክል መስማቱን ማረጋገጥ ፈለኩኝ፡ ማመን ከበደኝ ፣ ቀልድ መሰለኝ እንደውም ነገሩ በሆነ ሰአት የተሰማኝ ህመም ተመለሰ ፡ ይህ ቀልድ ነው እውነት? አይምሮዮ በሰኮንዶች ውስጥ ብዙ አሰበ ። እየተነገረ ያለው የይቅርታ ቃል ይልቅ የደረሰብኝ ሃዘን ገዝፎ ለመውጣት ታገለኝ። የሆነብኝን ነገር መናገር ጀመርኩ ወዲያው ግን ተመለስኩ ይቅርታ በመተው እንጂ በደልን በመቁጠር አይፈታም። እሺ ይቅር ብያለሁ ተውኩ አልኩ።

ምን አልባት አንተ አንቺ ይህን ስታነቢ በፍፁም ይቅር አልልም ያልሽበት ጉዳይ ይኖር ይሆን? ያንን ሰው ወይንም ወቅት በሃሳብ ላይ ሲመጣ ህመም ይሰማል? ሃዘን፡ ንዴት ይፈራረቅ ይሆን? እንግዲያው መፍትሄው አንድ ነው ሌላ መድሃኒት የለውም ይቅርታ ይባላል።

ማቲዎስ 5:7
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና

እናም ሰውን ይቅርታ መጠየቅ መታደል ነው አንድ አንዴ ነገሩ የባሰ ቢመስል እንክዋን መንፈስ ልብን እንዲጠግን ተስፋ አድርጎ ማለፍ ያስፈልጋል። አሁን ያሰው ያኔ ይቅርታ ስጠይቀው ለምን እንደተናደደብኝ ገብቶኛል ለዛ ሰው አብዝቼ መፀለይ ነበረብኝ በራሱ አቅም ይቅርታን ሊሰጥ አይችልም እና አልፈርድበትም። ምን አልባት ዳግም ባገኘው ያን ሰው ሰላም በዝቶለት እንዳይ እመናለሁ።

በህይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነገር፡ ግን ለብዙዎች የሚከብድ ቢኖር ይቅርታ ነው። አምላክ እራሱ በአካል መጥቶ ማስተማር የተጠበቀበት ለዚሁ ይመስለኛል። እናንተስ ምን ትላላችሁ ይቅርታ ጠይቃችሁ አለያ ተጠይቃችሁ ታውቁ ይሆን

Do you really deserve it all?

Is it really you are entitled to get everything? I usually here some speakers saying you are! You can do anything! You deserve it!

Really? I question that?

Are you trying to ascend to heavens to be like god’s or you know your places, you know you are placed to domain not to own!

There is clear fine line between bousting up to reach heaven , and humbly receiving the gift., where are you standing? Which one are you?

What you deserve is punishment, “for the wage of sin is death”. But someone took that payment for you. That put you free man!.

Because of this you are allowed to share the gifts. You did noting to create them!, they were made by someone, every living things and non living things around you looks up to the creater, they are a countable to Him. They don’t answer to you they only answer to Him, it is amazing how “HE” deleget things, As a free man you are responsible to take good care for them, because of the job description some power and Authority is imposed on you. this is why nature will respond to you.


ሁሉ ነገር የተሰጠን ከምህረት እጁ ውስጥ እንጂ ይገባን ዘንድ ያደረግነው አንዳች ነገር የለም። ሁሉ በእርሱ ለእርሱ የሆነው እንዲሁ በነፃ ሰጠን እንጂ።

ለአንተ ወይንም ለአንቺ ጥቅም ብቻ የሚውል የተሰጠ አዲስ ስልጣን የለም። ነገርግን የመንግስቱን ክብር ግርማ ወግ ስርአት ለመግለጥ ተሰጠ እንጂ ።

ሁሉ ይታዘዝለት ዘንድ የተቻለው ያንኑ ስልጣኑን አካፈለን : ይህ ማለት ግን እንድንጎርር ወይንም እንድንኩራራ ሳይሆን እርሱ በልቡ ትሁት ነው እና የእርሱን እግር ተከትለን መልካሙን የመንግስት አስተዳደር እንድንፈፅም ነው።

አንድ ግለሰብ እራሱን ብቻ እያሰበ ስልጣን ተሰጥቶኛል አቅም አለኝ ወዘተ — ቢለፈልፍ ኪሳራ ነው። ወይንም ደግሞ ጉዳዩ ከዘላለም መንግስት ጋር ግንኙነት የለውም። ይህ የተለቀቀው ኃይል መንግስትን ለመግለጥ ነውና ፡ የሰማይ መንግስት ደግሞ ሁሉን ይገዛል ለባሮቹም የተካፈለው ስልጣን ከሃላፊነት ጋር ነው

እግዚአብሔር የሰጠኝን ምህረት፣ ህይወት ፣ ስልጣን እንዲህ በቀልድ አልይዘውም በትህትና እና እርሱን በመፍራት እንጂ

እውነትን መናገር

በመንገድ ላይ ካየሁት ተነስቼ ብቻ ባወራ በእርግጥ የልምዴን እናገር ይሆናል ይህ ብቻ ግን የታሪክን ሙሉ እውነት አይገልፅም። አንዳንዱን እንደውም ስለረሳሁት ወይንም ላያስፈልግ ይችላል ከሚል ግምት ልዘለው እችላለሁ። ገጥሞአችሁ ያውቅ ይሆን የሆነ የምታውቁት ሰውን መንገድ ላይ አይታችሁት: ምን አልባት በርቀት ወይም በችኮላ ይሆንባችሁና ሳታናግሩት አልፋችሁ። ያን ሰው ስታገኙት በዚህ ቀን እዚህ ቦታ አየሁህ ስትሉ ያሰው በፍፁም በዛ ስፍራ እንዳልነበር ሲያስረዳችሁ? ወይንም እንዳያችሁት ስልክ ደውላችሁ እያየሁህ እኛ ለፍከኝ እንዲህ ቦታነኝ ስትሉ ያሰው ጭራስ ሌላ ክፍል ስፍራ መሆኑን ሲያረጋግጥላችሁ። ታዲያ ምን ትንሽ ፈጠረ? ያያችሁት ማንን ነው? ብዚ ጊዜ እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ዝም ብለን እንደ ተራ እናልፋቸዋለን። ነገርግን በእርግጥ ብናስተውላቸው ሌላ እውነት አላቸው ተምረባቸው እንድናልፍ የሚጠበቅ እውነት። ያየነው ብቻውን በቂ አይደለም።

አስታውሳለሁ የህግ መፅሃፍትን አገላብጥ ዘንድ እድል በነበረኝ ወቅት መምህራችን እንዲህ ይል ነበር “መስመሩ ላይ ያለውን ብቻ እኛ ታንብቡ ከመስመሩ በታች፣ ከመስመሩ በላይ ከመስመሩ በስተጀርባ የተፃፈውን ፈልጉ” እንዴት ያለ ትእዛዝ ነው? እኔ “የተፃፈውን እንጂ ያልተፃፈውን ከየት አምጥተን እናነባለን?” ያው መምህር ስለሚከበር በፊቱ አላጉረመረምኩም በልቤ እንጂ ።

በእርግጥም እውነት ለካ እንዲህ ናት አንዳንዴ ፊትለፊት ያለው የተገለጠው ብቻ ሳይሆን ያልተገለጠ የሚመስል ነገርግን ግልጥ የሚመስለውን የሚመራ እና የሚያስተናብር እውነት አለ።

በህግ ትምህርት ላይ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ለማየት ህግ አውጪዎቹ እነማን ናቸው? መቼ ነው ይህግ የወጣው? በዚህ ህግ መውጣት ጊዜ ምን ምን አይነት ክርክሮች ውይይቶች ተደርገው ነበር? ይህ ከመውጣቱ በፊት በምን ሁኔታ ነበር ጉዳዩ የሚታየው? ወደፊትስ ሊሸፍን የሚፈልገው ክልል አለወይ? እንግዲህ አንድ ህግ የሚለውን ለማወቅ ነው ይህ ሁሉ ምርምር: በእርግጥም በጥንቃቄ መረዳቱ ለሎሎች ህይወት ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችል አቅም ነውና ትክክለኛው ሃሳብ ማግኘት ግድያደርገዋል።

በህይወት ውስጥም እውነትን መፈለግ ከዚህ የባሰ ዝርዝር እይታ ይጠይቃክ ። ፊታችን ላይ እየሆነ ያለውን ብቻ ሳይሆን ከዛ አልፈን ማየት ይጠይቃል። ግለሰቦችን በውሳኔዎቻቸው እንዳንፈርፍባቸው ወይም የራሳችን እርምጃዎች ጠባብ በሆነ መንገድ ውስጥ እንዳይገኝ እውነትን መከታተል መልካም ነው።

የሐንስ 8:32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።

እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ

ይድረስ ለምወድህ እና ለማከብርህ እግዚአብሔር: እኔ ደህና ስለሆንኩና ስለተጠብኩ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ላይ ስልጣን ያለህ እንደሆንክ ስለማውቅ በደስታ ይህን እፅፍልሃለሁ።

My letter to you Lord

ለመሆኑ በህይወት መዝገብ ውስጥ ቀላል የሚባል የህይወት ጉዞ አለን? እንደው መንገዱ አልጋ በአልጋ የሆነለት ማን ይሆን? እኔን አይመስለኝም እያንዳንዱ ሰው የሚያልፍበት መንገድ የራሱ ኮረብታ ቁልቁለት ሜዳ ይኖረዋል። ” የ ይስሐቅን ህይወት ተመልክቼ ከ ወገኖቹ አንፃር ሲታይ ቀለል ያለ ህይወት የኖረ ይመስላል ነገርግን በደንብ ሲታይ ብዙ ግፊያ የነበረበት ህይወት ነው ። ማሳረፍን እምታውቅ አንተ ብታሳርፈውም”

በእርግጥ ለአንዳንዶቻችን ከባድ የሚመስሉ መንገዶች ይሰጡን እና እንዴት እንደምናልፋቸው ስንጨነቅ ገና ቀኑ ሳይደርስ ሃይላችንን እንጨርሳለን። የትግስትን ፍሬ ለማየት የቻለ ምንኛ እድለኛ ነው። “የዳዊት ህይወት ያሳዝናል በብዙ ስደት ፣ መገፋት፣ ከሞት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ነው። ምንአልባት በነዚህ የስደት ዘመናት ይህ ሰው መጠራቱን መቀባቱን ተጠራጥሮ ይሆናል: የመከራው ርዝመት ተስፋ የሚያስቆርጡ ወቅቶች ጋር መጋፈጡ ቀላል አልነበረም ነገርግን አምላክ ከተናገረው ህይወቱ ላይ ያልተከናወነ አልነበረም ”

እኔ እራሴ ነገር ቀለል ብሎልኝ የኖርኩባቸውን ዘመናት አስብና እንዴት እግዚአብሔር መልካም ነው እላለሁ : በዛው ልክ አላልፍም ብዬ ተስፋ የቆረጥኩባቸው ተራሮች ጋር እፋጠጣለሁ በዚህኛውም እግዚአብሔር መልካም ነው። የተራራው መትለቅ ወይም ማነስ ሳይሆን የአምላክ ማንነቱ ስለሆነ ስልጣን ያለው በዚህ ተስፋ ደስ እሰኛለሁ።

ቆይ ግን ደብዳቤው ለእግዚአብሔር አልነበር እንዴ መፃፍ የጀመርኩት እንዴት ሆኖ ነው የህይወት ውጣ ውረድ መዝገብ ውስጥ የገባሁት ? ለነገሩ ህይወትን እራሱ የያዝከው አንተ ስለሆንክ በውስጡ ያከሁት እኔ የገባኝን ባወራልህ ትክክል እንጂ ስህተት አይሆንም።