የተዋጀ ህይወት

ምን አልባት በይወታችን ብዙ ልንደርስባቸው እምናስበው እና እምንጥረው ነገር ይኖራል: ለአንዳንዳችን እጅግ እሩቅር እና የማንደርስበት ህልም ይመስላል በእርግጥ ህልም ነውን? እንደምናስበውስ ህይወት እንዲህ እሩቅናትን? በፍጹም በፍፁም አይደለም።

ህይወት በተሰጠን ቀን፣ ሰአት፣ ደቂቃ፣ ሰከንድ፣ ማይክሮሰከንድ ተጠቅላ እዚህ እና አሁን በሚባል እውነት ውስጥ ናት, አጠገባችን።

ህይወትን ዛሬ ላይ ማየት እና መቀበል ካልቻልን በህልም ውስጥ ስንኖር ዘመናችን ያልቃል። ነገ ለመኖር መጠበቅ፣ ነገ ገንዘብ ሳገኝ፣ ነገ ሲሳካልኝ፣ ነገ የሚባል ህልም ውስጥ እንወጣ ዘንድ ይሁን።

ዛሬ የሚባለውን ቀን እናደንቀው ዘንድ እንዲህ ተፃፈ ” ይህች ቀን ናት ጌታ የሰራት በእርሷ ኃሴት እናድርግ ደስም ይበለን”

ለነገ እምናስቀምጠው ህይወት እና ደስታ የለም። ዛሬ አሁን መኖር ነው ትርፍ።

በአንድ ወቅት አንድ ሰው በህይወት ላይ ትልቁ ነገር ፣ውዱ እና አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው ብሎ ጠየቀ ከነበርነው ወጣቶች መካከል ሁሉም የራሱን ሃሳብ ሰጠ። ማንም ግን አፍንጫው ስር ያለውን እውነት አላስተዋለም ነበር ። ጠያቂው እስትንፋስ ሳትተነፍሱ ትኖራላችሁን የሚል አይነት ጥያቄ አቀረበ በእርግጥ ለካ ካልተነፈስን የሚቀጥል ነገር የለም።

ወደዚህ ምድር ስንመጣ ወደ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳብነው አየር ይህችን ምድር ስናልፍም የመጨረሻውን አየር አስወጥተን እናልፋለን በዚህ እስትንፋስ ሂደት ውስጥ ህይወት አለች። ‘እኔ ሁሌ እገረማለሁ በዚህ እውነት’

ትንሽ ቆይቼ ሌላ እውነት ተማርኩ ለካ እጅግ ውዱ እና አንገብጋቢው ነገር መፅሃፍ ከእስትንፋስ ይልቅ የሚጠጋጋ ብሎ የሚጠራው እውነት አለ።

በአካል ከሚታየው የሚሻገር እውነት።

ከእስትንፋስ ይልቅ የሚጠጋጋ በህይወት ያኖረኛል

Leave a comment